JM Building Services - шаблон joomla Продвижение

ኮንትራክተር ሁነው የሰራተኞች የእውቀት አቅም አስጨንቆዎት ከሆነ፣ ወይም መንግስታዊ ያልሆነ የተራድዖ ድርጅት እየመሩ የሚደግፏቸው ወጣቶች ዘለቄታዊ ህይወት ካሳሰበዎች፣ ወይም የመንግስት ተቋም እየመሩ የሚመሯቸው ሰራተኞች በትርፍ ጊዜያቸው እውቀት እንዲገበዩ ከፈለጉ? ኢ ኤም ዲ የዘመናዊ ህንጻ የፊኒሽንግ ሙያ ማሰልጠኛ ተቋም በቡድን እና በተናጥል ለሚመጡ ወጣቶች ልዩ ፕሮግራም አለው። እስካሁን ድረስም ወጣቶችን በመላክ ከኢ ኤም ዲ ጋር እየሰሩ የሚገኙ ተቋማት

የእናቶች እና ህጻናት ዘርፈ ብዙ የልማት ድርጅት
መርካቶ የህጻናት መርጃ ማዕከል
ዶርከስ ኢትዮጵያ
በየካ ክፍለከተማ ወረዳ 05 ወጣቶች ማዕከል
በኢፌዲሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና ሌሎችም ይገኛሉ።

በተጨማሪም ኢ ኤም ዲ በራሰዳቸው ከፍለው መማር ለማይችሉ ከተለያዩ ተቋማት ለሚመጡ ሰራተኞች የነጻ ስልጠና እድል የሚሰጥ ሲሆን በ2008 በመጀመሪያ ዙር ለጀመርነው ስልጠና ለ10 ሰልጣኞች ነጻ የትምሀርት እድል ሰጥቷል። 
ለጥያቄዎት 0920016423 ይደውሉ።